La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዮሐንስ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርን ያየ ከቶ ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ ግን እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርን ያየው ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፥ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርን ያየው ማንም ሰው የለም። እኛ እርስ በርሳችን ብንፋቀር እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።

Ver Capítulo



1 ዮሐንስ 4:12
14 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ስፍራ ባረ​ከው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ዳነች” ሲል የዚ​ያን ቦታ ስም “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ሰው አይ​ቶኝ አይ​ድ​ን​ምና ፊቴን ማየት አይ​ቻ​ል​ህም” አለ።


እኔ አፍ ለአፍ በግ​ልጥ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በስ​ው​ርም አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ያያል፤ አገ​ል​ጋዬ ሙሴን ማማ​ትን ስለ ምን አል​ፈ​ራ​ች​ሁም?” አለ።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


አሁ​ንም እነ​ዚህ ሦስቱ እም​ነት፥ ተስ​ፋና ፍቅር ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤ ከሁሉ ግን ፍቅር ይበ​ል​ጣል።


ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤ ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና።


ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤


ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።


እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።


ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?


እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።