1 ዮሐንስ 3:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዞቹንም የሚጠብቁ ሁሉ በርሱ ይኖራሉ፤ እርሱም በእነርሱ ይኖራል። በእኛ መኖሩን በዚህ፣ ይኸውም እርሱ በሰጠን መንፈስ እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዙን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በእኛ እንደሚኖር በዚህ እናውቃለን፥ ይኸውም በሰጠን በመንፈሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚፈጽሙ ሁሉ በእግዚአብሔር ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ይኖራል። እግዚአብሔር በእኛ መኖሩን የምናውቀው እርሱ በሰጠን መንፈስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን። |
እርሱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ ይኖራልና፤ ያድርባችሁማልና።
ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ አብ በእኔ እንዳለህ፥ እኔም በአንተ እንዳለሁ፥ እነርሱም እንደ እኛ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ።
እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንፈስም በእናንተ ላይ አድሮ እንደሚኖር አታውቁምን?
ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር ለተቀበላችሁት በእናንተ አድሮ ላለ ለመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ለራሳችሁም አይደላችሁም።
የእግዚአብሔርን ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደሪያዎች እኛ አይደለንምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ፤ በመካከላቸውም እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል።”
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።