La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ሁሉ የሚ​ያ​ው​ቀው አይ​ደ​ለም፤ እስከ ዛሬ በጣ​ዖ​ታት ልማድ፥ ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን የሚ​በሉ አሉ፤ ኅሊ​ና​ቸ​ውም ደካማ ስለ​ሆነ ይረ​ክ​ሳል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ይህን የሚያውቁ ሁሉም አይደሉም፤ አንዳንድ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ፣ እንዲህ ያለውን ሥጋ ሲበሉ በርግጥ ለጣዖት እንደ ተሠዋ ያስባሉ፤ ኅሊናቸውም ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ይህ ዕውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፥ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤ ብለው ይበላሉና፥ ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ይህን የሚያውቁ፥ ሁሉም አይደሉም፤ አንዳንዶች እስከ አሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ ሥጋን የሚበሉት ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ነው፤ ስለዚህ ኅሊናቸው ደካማ በመሆኑ ይረክሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ይህ እውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት የተሠዋ ነው ብለው ይበላሉና ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 8:7
11 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እን​ደ​ሌለ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ሆኜ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ተረ​ድ​ቼ​አ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ማና​ቸ​ውም ነገር ርኩስ እን​ደ​ሚ​ሆን ለሚ​ያ​ስብ ያ ለእ​ርሱ ርኩስ ነው።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔም በጎ ምግ​ባ​ርን ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ፈ​ጽሙ እታ​መ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ ፍጹም ዕው​ቀ​ትን የተ​መ​ላ​ችሁ ናችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም ልታ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ትች​ላ​ላ​ችሁ።


ደግ​ሞም በሥጋ ገበያ የሚ​ሸ​ጡ​ትን ሁሉ ከሕ​ሊና የተ​ነሣ ሳት​መ​ራ​መሩ ብሉ።


ለጣ​ዖ​ታት ስለ​ሚ​ሠዉ መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ሁላ​ች​ንም ዕው​ቀት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን፤ ዕው​ቀት ያስ​ታ​ብ​ያል፤ ፍቅር ግን ያን​ጻል።


ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።