ስለዚህም እርስዋን መቃወም የሚቻለው ያለ አይመስለኝም፤ አሁንም ይህን በጠብና በክርክር ሳይሆን በቀስታ ልናደርገው ይገባናል።
1 ቆሮንቶስ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መታገሥ ባይችሉ ግን ያግቡ፤ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት ካልቻሉ ያግቡ፤ በምኞት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በመሻት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ካልቻሉ ያግቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በሥጋ ምኞት ከመቃጠል ይልቅ ማግባት የተሻለ ነውና ራሳቸውን መቈጣጠር ቢያቅታቸው ያግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ። |
ስለዚህም እርስዋን መቃወም የሚቻለው ያለ አይመስለኝም፤ አሁንም ይህን በጠብና በክርክር ሳይሆን በቀስታ ልናደርገው ይገባናል።
ብታገባም ኀጢአት አይሆንብህም፤ ድንግሊቱም ባል ብታገባ ኀጢአት አይሆንባትም፤ ያገቡ ግን ለራሳቸው ድካምን ይሻሉ፤ እኔም ይህን የምላችሁ ስለማዝንላችሁ ነው።
በሸመገለ ጊዜ ስለ ድንግልናው እንደሚያፍር የሚያስብ ሰው ቢኖር እንዲህ ሊሆን ይገባል፤ የወደደውን ያድርግ፤ ቢያገባም ኀጢአት የለበትም።
ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሠረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወደደችውን ታግባ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ይሁን።
ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤