ከእርስዋም ሌላ ቢያገባ፥ ቀለብዋን፥ ልብስዋንም፥ ለጋብቻዋም ተገቢውን ይስጣት፤ እንዳልበደላትም ምስክር ያሰማባት።
1 ቆሮንቶስ 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚስትም ባልዋ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንዲሁ ሚስትም ለባልዋ የሚገባውን ታድርግለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባል ለሚስቱ የሚገባትን ሁሉ ያድርግላት፤ ሚስትም ለባሏ እንዲሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስት ለባሏ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን የጋብቻ መብትዋን አይከልክላት፤ እንዲሁም ሚስት ለባልዋ ማድረግ የሚገባትን የጋብቻ መብቱን አትከልክለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ። |
ከእርስዋም ሌላ ቢያገባ፥ ቀለብዋን፥ ልብስዋንም፥ ለጋብቻዋም ተገቢውን ይስጣት፤ እንዳልበደላትም ምስክር ያሰማባት።
ሚስት በራስዋ አካል ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል በራሱ አካል ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።