1 ቆሮንቶስ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛ “የጥበበኞች አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል” ብሎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌላ ስፍራ ደግሞ፣ “ጌታ የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል” ተብሎ ተጽፏል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም “ጌታ የጥበበኞችን ሐሳብ ከንቱ እንደሆነ ያውቃል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም፥ “ጌታ የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ መሆኑን ያውቃል” የሚል ተጽፎአል። |
እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም፤ አላመሰገኑትምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአሳባቸውም ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ጨለመ።
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።