1 ቆሮንቶስ 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እኛስ ሁልጊዜ መከራን ስለምን እንቀበላለን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛስ ብንሆን ዘወትር ለአደጋ የምንጋለጠው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛስ ብንሆን ዘወትር ለአደጋ የምንጋለጠው ለምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛስ ብንሆን በየሰዓቱ ለአደጋ እየተጋለጥን የምንኖረው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው? |
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነውና በእናንተ ላይ ባለኝ ትምክህት ሁልጊዜ እገደላለሁ።
እንደማይታወቁ ስንታይ የታወቅን ነን፤ እንደ ሰነፎች ስንታይም ልባሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስንታይ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆንም አንገደልም።
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ግዝረትን ገና የምሰብክ ከሆነ፥ እንግዲህ ለምን ያሳድዱኛል? እንግዲህ የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት እንዲያው ቀርቶአል።