1 ቆሮንቶስ 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እናንተ በማይታወቅ ቋንቋ ብትናገሩ፥ ይህንኑም ገልጣችሁ ባትተረጕሙ የምትሉትንና የምትናገሩትን ማን ያውቃል? ከነፋስ ጋር እንደምትነጋገሩ ትሆናላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ ከአንደበታችሁ ትርጕም ያለው ቃል ካልወጣ፣ የምትናገሩትን ማን ሊያስተውለው ይችላል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ ከአንደበታችሁ የሚታወቅ ቃል ካልወጣ፥ የምትናገሩትን ማን ሊያስተውለው ይችላል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እናንተ በቋንቋ ስትነጋገሩ ግልጥ በሆኑ ቃሎች ካልተናገራችሁ የምትናገሩትን ማን ሊያውቀው ይችላል? ለነፋስ እንደምትናገሩ ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ ሰዎች የምትናገሩትን እንዴት አድርገው ያስተውሉታል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁና። |