1 ቆሮንቶስ 14:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሴት በቤተ ክርስቲያን መናገር ክልክል ነው፤ ሊማሩ ከወደዱ ደግሞ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፥ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በቤተ ክርስቲያን መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ነገርን ማወቅ ቢፈልጉ ባሎቻቸውን በቤታቸው ይጠይቁ፤ በጸሎት ስብሰባ ጊዜ ሴት እንድትናገር ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ። |
እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።