ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”
1 ቆሮንቶስ 14:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶችም በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ፤ ሊታዘዙ እንጂ ሊናገሩ አልተፈቀደምና፤ ኦሪትም እንዲህ ብሎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቶች በጉባኤ ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶች በጸሎት ስብሰባ ጊዜ ዝም ይበሉ፤ ሕግ እንደሚያዘው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና። |
ለሴቲቱም እግዚአብሔር አላት፥ “ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ከወለድሽም በኋላ ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ይገዛሻል።”
ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራሱ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስዋ ወንድ፤ የክርስቶስም ራሱ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወድዳለሁ።
ራስዋን ሳትከናነብ የምትጸልይ ወይም የምታስተምር ሴት ሁላ ራስዋን ታዋርዳለች፤ ራስዋን እንደ ተላጨች መሆንዋ ነውና።
በኦሪትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አንደበት እናገራቸዋለሁ፤ እንዲሁም ሆኖ አይሰሙኝም ይላል እግዚአብሔር” ብሎአል።