ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ፥ በሌሎች አሕዛብ እንደ ሆነ በእናንተም ዋጋዬን አገኝ ዘንድ ሁልጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንደ ወደድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረስም እንደ ተሳነኝ ልታውቁ እወድዳለሁ።
1 ቆሮንቶስ 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አላዋቆች ልትሆኑ አንወድድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ አሁን ደግሞ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይህን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ! አላዋቂ እንድትሆኑ አልፈልግም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! አሁን ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እንድታውቁ እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። |
ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ፥ በሌሎች አሕዛብ እንደ ሆነ በእናንተም ዋጋዬን አገኝ ዘንድ ሁልጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንደ ወደድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረስም እንደ ተሳነኝ ልታውቁ እወድዳለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ አባቶቻችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረዳቸው ሁሉም በባሕር መካከል አልፈው እንደ ሄዱ ልታውቁ እወዳለሁ።
ራሱን እንደ ነቢይ አድርጎ ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት አድርጎ የሚቈጥር ቢኖር፥ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነውና ይህን የጻፍሁላችሁን ይወቅ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በእስያ መከራ እንደ ተቀበልን ልታውቁ እወዳለሁ፤ ለሕይወታችን ተስፋ እስክንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ እጅግ መከራ ጸንቶብን ነበርና።
እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦቹም ሐዋርያትን፥ ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን፥ ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ።
እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።