1 ቆሮንቶስ 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ፥ አመሰግናችኋለሁ፤ ዘወትር ታስቡኛላችሁና፤ ያስተማርኋችሁንም ትምህርት ጠብቃችኋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁሉም ነገር ስለምታስቡልኝና ከእኔ የተቀበላችሁትን ትምህርት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! በሁሉ ስለምታስቡኝና እኔ ያስተላለፍኩላችሁን ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘወትር ስለምታስታውሱኝና የሰጠኋችሁንም ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ፥ አመሰግናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። |
ይህንም የነገርኋችሁ ላመሰግናችሁ አይደለም፤ በምትሰበሰቡበት ጊዜ ወደ ዝቅተኛ እንጂ ወደሚሻል ግብር አትሄዱምና።
በውኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ታስነቅፋላችሁን? ነዳያንንስ ታሳፍሩአቸዋላችሁን? ምን እላለሁ? በዚህ አመሰግናችኋለሁን? አላመሰግናችሁም።
ስለዚህም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዳስተማርሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የሄድሁበትን መንገድ ይገልጥላችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር የታመነና ልጄ ወዳጄ የሆነ ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ።
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ የምሥራች ብሎ በነገረን ጊዜ፥ እኛም እናያችሁ ዘንድ እንደምንናፍቅ ታዩን ዘንድ እየናፈቃችሁ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስቡን በነገረን ጊዜ፥
ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።