La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ የም​ን​ባ​ር​ከው የበ​ረ​ከት ጽዋ ከክ​ር​ስ​ቶስ ደም ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን? የም​ን​ፈ​ት​ተው ይህስ ኅብ​ስት ከክ​ር​ስ​ቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋራ ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋራ ኅብረት ያለው አይደለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምንባርከው የበረከት ጽዋ፥ የክርስቶስን ደም መካፈል አይደለምን? የምንቆርሰውስ ኀብስት፥ የክርስቶስን ሥጋ መካፈል አይደለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኛ እግዚአብሔርን አመስግነን የምንካፈለው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰው ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 10:16
17 Referencias Cruzadas  

ጽዋ​ው​ንም ተቀ​ብሎ አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህን እንኩ ሁላ​ች​ሁም ተካ​ፈ​ሉት።


በሐ​ዋ​ር​ያት ትም​ህ​ር​ትና በአ​ን​ድ​ነት ማዕ​ድን በመ​ባ​ረክ፥ በጸ​ሎ​ትም ጸን​ተው ይኖሩ ነበር።


ሁል​ጊ​ዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅ​ደስ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በቤ​ትም ኅብ​ስ​ትን ይቈ​ርሱ ነበር፤ በደ​ስ​ታና በልብ ቅን​ን​ነ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይመ​ገቡ ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሰገ​ነት ወጣ፤ ማዕ​ዱ​ንም ባርኮ በላ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብዙ ትም​ህ​ርት አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚያ በኋ​ላም ተነ​ሥቶ ሄደ።


ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመ​ባ​ረክ ተሰ​ብ​ስ​በን ሳለን ጳው​ሎስ በማ​ግ​ሥቱ የሚ​ሄድ ነውና ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመረ፤ እስከ መን​ፈቀ ሌሊ​ትም ድረስ ትም​ህ​ር​ቱን አስ​ረ​ዘመ።


ከልጁ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠ​ራ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው።


ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ደ​ሚ​ነ​ገር እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ው​ንም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


እኛ ሁላ​ች​ንም በአ​ንድ መን​ፈስ አንድ አካል ለመ​ሆን ተጠ​ም​ቀ​ናል፤ አይ​ሁድ ብን​ሆን፥ አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብን​ሆን፥ ባሪ​ያ​ዎ​ችም ብን​ሆን፥ ነጻ​ዎ​ችም ብን​ሆን ሁላ​ችን አንድ መን​ፈስ ጠጥ​ተ​ና​ልና።


በዚች ጽድቅ እስከ መጨ​ረሻ የቀ​ደ​መ​ውን ሥር​ዐ​ታ​ች​ንን አጽ​ን​ተን ከጠ​በ​ቅን ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ሁነ​ና​ልና።


እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።