የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
1 ዜና መዋዕል 6:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ታቦቷ በምታርፍበት ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በጌታ ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት ለሚያገለግሉት መዘምራን ኀላፊ የሚሆኑ ሰዎችን ሾመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።
ዳዊትም፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ሌዋውያንም ሁሉ፥ መዘምራኑም፥ የመዘምራኑም አለቃ ኮኖንያስ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብሰው ነበር፤ ዳዊትም የከበረ ልብስ ለብሶ ነበረ።
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በምስክሩ ድንኳን ማደሪያ ፊት በበገና እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ለአገልግሎታቸው ይቆሙ ነበር።
ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን በየሰሞናቸው አገልጋዮችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረ።
አናጢዎቹም የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠሩ ዘንድ መሠረት በጣሉ ጊዜ ካህናቱ ልብሳቸውን ለብሰው መለከቱን ይዘው፥ የአሳፍም ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው እንደ እስራኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥርዐት እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ።
ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ፤ እነሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ደቡብ ይመለከት ነበረ፤ ሌላውም ወደ ደቡብ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።