1 ዜና መዋዕል 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴሞንም ልጆች አምኖን፥ የአናን ልጆች ሬኖንና ቲሎን ነበሩ፤ የይስቴም ልጆች ዘካትና የዘካት ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤን-ሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢን-ዞሔት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሺሞንም አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናንና ቲሎን ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። ዩሽዒም ዞሔትና ቤንዞሔት ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆች ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ። |