1 ዜና መዋዕል 27:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ነጦፋዊው መዐርኢ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐሥረኛው ወር፣ ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ማህራይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሥረኛው ወር አሥረኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ነጦፋዊው ኖኤሬ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ነጦፋዊው ኖኤሬ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። |
በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው አለቃ ከብንያማውያን የነበረው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
በዐሥራ አንደኛው ወር ዐሥራ አንደኛው አለቃ ከኤፍሬም ልጆች የነበረው ፍርዓቶናዊው በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።