1 ዜና መዋዕል 26:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የለአዳን ልጆች፤ ለለአዳን የሆኑ የጌድሶናውያን ልጆች፥ ለጌድሶናዊው ለለአዳን የሆኑ፥ የአባቶች ቤቶች አለቆች ይሔኤሊ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የለአዳን ዘሮች፣ በለአዳን በኩል ጌርሶናውያን የሆኑትና ለጌርሶናዊው ለለአዳን ቤተ ሰቦች አለቆች የሆኑት የለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የለአዳን ልጆች፤ የለአዳን ቤተሰብ የሆኑ የጌድሶናውያን ልጆች፥ ለጌድሶናዊው ከለአዳን ቤተሰብ የሆኑ የአባቶች ቤቶች አለቆች ይሒኤሊ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላደን ከጌርሾን ጐሣ የነበረ ሲሆን እርሱም የይሒኤል አባት ነበር፤ ከእርሱ ተወላጆች ብዙዎቹ በየወገናቸው የቤተሰብ አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለአዳን ልጆች፤ ለለአዳን የሆኑ የጌድሶናውያን ልጆች፥ ለጌድሶናዊ ለለአዳን የሆኑ የአባቶች ቤቶች አለቆች ይሒኤሊ፤ |
ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር።