እንደማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን፥ ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።
1 ዜና መዋዕል 22:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፤ መንግሥትህንም በእስራኤል ላይ ያጽና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤል ላይ አለቃ ባደረገህ ጊዜ፣ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻ የአምላክህን የጌታን ሕግ እንድትጠብቅ ጌታ ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሰልጥንህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤል ላይ ሥልጣን በሚሰጥህ ጊዜ ያምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ ጥበቡንና ማስተዋሉን ይስጥህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፤ በእስራኤልም ላይ ያሰልጥንህ። |
እንደማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን፥ ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።
አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና ማስተዋልን ስጠኝ፤ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ መፍረድ የሚቻለው የለምና።”
ጠብቁት፤ አድርጉትም፤ ይህን ሥርዐት ሁሉ ሰምተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤