1 ዜና መዋዕል 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለነቢዩ ለጋድ እንዲህ አለው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም የዳዊት ባለራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ለዳዊት ባለ ራእይ ለጋድ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የዳዊት ነቢይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ለዳዊት ባለ ራዕይ ለጋድ |
“ሂድ፥ ለዳዊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ ብለህ ንገረው።”
እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል በንጉሡ ፊት የሚዘምረው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና፥ መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት አቆመ።
ነቢዩ ጋድም ዳዊትን፥ “ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአንባው ውስጥ አትቀመጥ” አለው፤ ዳዊትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተማም መጥቶ ተቀመጠ፤
ቀድሞ ነቢዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እንሂድ ይል ነበር።”