የአቢሱርም ሚስት ስም አቢካኤል ነበረ፤ እርስዋም፥ አዛቡርንና ሞሊድን ወለደችለት።
የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
የአቢሱርም ሚስት አቢካኢል ትባል ነበር፤ አሕባንንና ሞሊድን ወለደችለት።
አቢሹርም አቢኃይል ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት አግብቶ አሕባንና ሞሊድ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤
የአቢሱርም ሚስት አቢካኢል ነበረች፤ አሕባንንና ሞሊድን ወለደችለት።
የአናምም ልጆች ሸማይና ያዳይ ነበሩ። የሸማይም ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ።
የናዳብም ልጆች ሴሌድና አፋይም ነበሩ፤ ሴሌድም ልጆችን ሳይወልድ ሞተ።