ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወደ አገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉብንም ወለደችለት።
1 ዜና መዋዕል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴጉብም ኢያኤርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠጉብም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩትን ጌሹርን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰጉብም ያኢር ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ያኢር በገለዓድ ግዛት ውስጥ የሚገኙትን ኻያ ሦስት ከተሞች ይገዛ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት። |
ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወደ አገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉብንም ወለደችለት።
ኤስሮምም ጌሱርንና አራምን የኢያዔርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰደ። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ከተሞች ነበሩ።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።
ድንበራቸውም ከመሐናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥ የገለዓድም እኩሌታ፥