Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሰጉብም ያኢር ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ያኢር በገለዓድ ግዛት ውስጥ የሚገኙትን ኻያ ሦስት ከተሞች ይገዛ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሠጉብም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩትን ጌሹርን ወለደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሴጉ​ብም ኢያ​ኤ​ርን ወለደ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተ​ሞች ነበ​ሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 2:22
7 Referencias Cruzadas  

ሔጽሮን ሥልሳ ዓመት ሲሞላው የገለዓድ እኅት የነበረችውን የማኪርን ልጅ አግብቶ ሰጉብ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤


ነገር ግን የገሹርና የአራም ነገሥታት ሥልሳ የሚያኽሉ ታናናሽ ከተሞችን ከዚያው ከገለዓድ ድል አድርጎ ያዘ፤ ይህም የያኢርንና የቀናትን መንደሮች እንዲሁም በአቅራቢያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች የሚያጠቃልል ነበር፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ናቸው፤


ስለዚህም ሙሴ የገለዓድን ምድር ለማኪር ቤተሰብ ሰጣቸው፤ እነርሱም በዚያ ኖሩ።


ከምናሴ ነገድ የሆነው ያኢር በአንዳንድ መንደሮች ላይ አደጋ ጥሎ ወሰዳቸው፤ “የያኢር መንደሮች” ብሎም ሰየማቸው።


ከምናሴ ነገድ ወገን የሆነው ያኢር መላውን የአርጎብ ምድር ወረሰ፤ ይህችውም እስከ ገሹርና እስከ ማዕካ ጠረፍ የምትደርሰው ባሳን ናት፤ መንደሮቹንም በእርሱ ስም እንዲጠሩ አደረገ፤ ስለዚህ እነርሱ የያኢር መንደሮች ተብለው እስከ ዛሬ ይጠራሉ።


“ገለዓድንም ከምናሴ ነገድ ወገን ለሆነው ለማኪር ቤተሰብ ሰጠሁ፤


ግዛታቸውም ማሕናይምንና ባሳንን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ይህም ባሳን መላውን የባሳን ንጉሥ የዖግን ግዛት እንዲሁም በባሳን በተለይ ያኢር ተብላ በምትጠራው ስፍራ የሚገኙትን ሥልሳ ከተሞች ሁሉ ይጨምራል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos