1 ዜና መዋዕል 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ልብህም ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ለእኔ አደረግህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ስለ ባርያህ ስትል እንደ ልብህ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ በማስታወቅ ይህን ተአምራት ሁሉ አድርገሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ታደርግልኝ ዘንድ እንዲሁም ወደፊት ታላቅ እንደምታደርገኝ ታስታውቀኝ ዘንድ በጎ ፈቃድህና ዕቅድህ ሆኖአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ! ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ታስታውቀው ዘንድ ስለ ባሪያህ እንደ ልብህም ይህን ተአምራት ሁሉ አድርገሃል። |
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።