ደግሞም በሮም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ የቤተልሔማዊውም የዓሬኦርጌም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎዶልያን ገደለው።
1 ዜና መዋዕል 11:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በጭፍሮቹ ዘንድ የነበሩት ኀያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም በሠራዊቱ ዘንድ የነበሩት ኃያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፥ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥ የሐሮድ ተወላጅ ሻሞት፥ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፥ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፥ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፥ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ዒላይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌድ፥ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሪባይ ልጅ ኢታይ፥ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፥ በጋዓሽ አጠገብ ባሉት ሸለቆዎች የተወለደው ሑራይ፥ የዓረባ ተወላጅ የሆነው አቢኤል፥ የባሕሩም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፥ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፥ የጊዞን ተወላጅ የሆነው ሃሼም፥ የሃራር ተወላጅ የሆነው የሻጌ ልጅ ዮናታን፥ የሀራር ተወላጁ የሳካር ልጅ አሒአም፥ የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ የመኬራ ተወላጅ የሆነው ሔፌር፥ የፐሎን ተወላጅ የሆነው አሒያ፥ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፥ የኤዝባይ ልጅ ናዕራይ፥ የናታን ወንድም ዮኤል፥ የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፥ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፥ የበኤሮት ተወላጅና የኢዮአብ ጋሻጃግሬ የነበረው ናሕራይ፥ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፥ ሒታዊው ኦርዮን፥ የአሕላይ ልጅ ዛባድ፥ የሺዛ ልጅ ዐዲና፤ (ይህ ሰው የራሱ ቡድን የሆኑ ሠላሳ ወታደሮችን እንደ ያዘ ከሮቤል ነገድ የታወቀ ነበር፤) የማዕካ ልጅ ሐናን፥ የሚታን ተወላጅ የሆነው ኢዮሣፍጥ፥ የዐሽተራ ተወላጅ የሆነው ዑዚያ፥ የዓሮዔር ተወላጅ የሆነው የሆታም ልጆች ሻማዕና ይዒኤል፥ የቲጺ ተወላጅ የሆነው የሺምሪ ልጆች ይዲዕኤልና ዮሐ፥ የማሐዋ ተወላጅ የሆነው ኤሊኤል፥ የኤልናዓም ልጆች ይሪባይና ዮሻውያ፥ የሞአብ ተወላጅ የሆነው ዩትማ፥ የጾባ ተወላጆች የሆኑት ኤሊኤል፥ ዖቤድና ያዕሲኤል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በጭፍሮች ዘንድ የነበሩት ኀያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥ |
ደግሞም በሮም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ የቤተልሔማዊውም የዓሬኦርጌም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎዶልያን ገደለው።
የዳዊት ኀያላንም ስማቸው ይህ ነው። የኢዮአብ ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአጎቱ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥
ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ይገድሉት ዘንድ ይጠባበቁ ነበር።
እነሆ፥ ከሠላሳው ይልቅ የከበረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በናያስን በሀገሩ ላይ ሾመው።
በአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሳሄል ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያና ወንድሞቹ ነበሩ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።