1 ዜና መዋዕል 11:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ በሦስቱ ኀያላን መካከል የነበረ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዛር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኀያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ በሦስቱ ኃያላን መካከል የነበረ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዛር ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ የሚቀጥል ከሦስቱ ኀያላን አንዱ የሆነው ሌላው ከአሖሕ ጐሣ የዶዶ ልጅ አልዓዛር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ በሦስቱ ኀያላን መካከል የነበረ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዛር ነበረ። |
ከእርሱም በኋላ የዳዊት የአጎቱ ልጅ የዱዲ ልጅ ኤልያናን ነበረ፤ ለሰልፍ የተሰበሰቡትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ከነበሩ ከሦስቱ ኀያላን አንዱ እርሱ ነበረ፤ የእስራኤልም ሰዎች ተመለሱ።
“ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይገባኝም፤ ሰውነታቸውንም ለሞት አሳልፈው አምጥተውታልና የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን?” አለ። ስለዚህም ዳዊት ይጠጣው ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኀያላን ያደረጉት ይህ ነው።
በሁለተኛውም ተራ በሆኑት በሦስቱ መካከል የከበረ ነበረ፥ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም።
በሁለተኛውም ወር ክፍል ላይ የኤቲ ልጅ ዶድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሚኮሎት አለቃ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።