1 ዜና መዋዕል 1:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ሳፍር፥ ጎታም፥ ቄኔዝ፥ ቴምናስ፥ አማሌቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሊፋዝም ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፊ፥ ጋዕታም፥ ቀናዝ፥ ቲምናዕና፥ ዐማሌቅ ተብለው የሚጠሩትን ልጆች ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ስዎች ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ ትንንሾች በጎችን ዘርፈው ይወስዷቸዋል፤ የሚኖሩባትንም ማደሪያቸውን ባድማ ያደርጉባቸዋል።
ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?