ሶፎንያስ 3:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢያቷ ትዕቢተኞች፣ አታላዮችም ናቸው፤ ካህናቷ መቅደሱን ያረክሳሉ፣ በሕግም ላይ ያምፃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢዮችዋ ስዶችና ከሐዲ ሰዎች ናቸው፥ ካህናቶቿ መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ አምፀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢያትዋ በትዕቢት የተወጠሩና በተንኰል የተሞሉ ናቸው፤ ካህናትዋ የተቀደሰውን ያረክሳሉ፤ በሕግም ላይ ያምፃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፣ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፥ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል። |
“እነሆ፤ ሐሰተኛ ሕልም ተመርኵዘው ትንቢት የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እኔ ሳልልካቸው ወይም ሳልሾማቸው ደፍረው ውሸት ይናገራሉ፤ ሕዝቤንም ያስታሉ፤ ለዚህም ሕዝብ አንዳች አይረቡትም” ይላል እግዚአብሔር።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”
ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤ ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤ ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣ ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤ ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤ ሁሉም ያጭበረብራሉ።
የነቢያቶችሽ ራእይ፣ ሐሰትና ከንቱ ነው፤ ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም። የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣ የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው።
ካህናቷ በሕጌ ላይ ያምፃሉ፤ ንዋያተ ቅድሳቴን ያረክሳሉ፤ የተቀደሰውን ከረከሰው አይለዩም፤ በጐደፈውና በንጹሑ መካከል ልዩነት እንደሌለ ያስተምራሉ፤ ሰንበታቴን ከማክበር ዘወር ብለዋል፤ በዚህም በመካከላቸው ተንቄአለሁ።
የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።
ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣ ‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።
መሪዎቿ በጕቦ ይፈርዳሉ፤ ካህናቷ ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ ነቢያቷም ለገንዘብ ይጠነቍላሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈውም፣ “እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይደርስብንም” ይላሉ።
“ልጅ አባቱን፣ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔ አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ካህናት ሆይ፤ ስሜን የምታቃልሉት እናንተ ናችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።
“ካህኑ የሁሉ ገዥ፣ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለ ሆነ ከንፈሮቹ ዕውቀትን ሊጠብቁ፣ ሰዎችም ከአንደበቱ ትምህርትን ሊፈልጉ ይገባል፤
እናንተ ግን ከመንገዱ ወጥታችኋል፤ በትምህርታችሁም ብዙዎች እንዲሰናከሉ አድርጋችኋል፤ የሌዊንም ኪዳን አፍርሳችኋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።
በዚህ ጊዜ ዔሊ እጅግ አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በመላው እስራኤል ያደርጉ የነበረውን፣ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋራ ዝሙት መፈጸማቸውን ሰማ።