ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን፣ “እነሆ፤ የመሞቻዬ ጊዜ ተቃርቧል፤ እግዚአብሔርም በረድኤቱ ይጐበኛችሁና ከዚህ አገር ያወጣችኋል፤ ለአባቶቻችን ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባችኋል” አላቸው።
ሶፎንያስ 2:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤ እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ። በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋል፤ ምርኳቸውንም ይመልስላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፤ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ፤ ጌታ አምላካቸው ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካቸው ስለሚንከባከባቸውና ንብረታቸውን ስለሚመልስላቸው ከብቶቻቸውን ያሰማሩበት ዘንድ የባሕሩ ዳር ከይሁዳ ሕዝብ ለተረፉት ርስት ይሆናል፤ በየምሽቱም በአስቀሎና ቤቶች ያድራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፣ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፥ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ። |
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን፣ “እነሆ፤ የመሞቻዬ ጊዜ ተቃርቧል፤ እግዚአብሔርም በረድኤቱ ይጐበኛችሁና ከዚህ አገር ያወጣችኋል፤ ለአባቶቻችን ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባችኋል” አላቸው።
በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።
እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤ እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤ በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል። መጻተኞች ዐብረዋቸው ይኖራሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋራ ይተባበራሉ።
ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣ የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰባው ዓመት የባቢሎን ቈይታችሁ በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ ልመልሳችሁ የገባሁላችሁን መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
እኔም እገኝላችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከምርኮም እመልሳችኋለሁ፤ እናንተንም ከበተንሁበት አገርና ስፍራ ሁሉ እመልሳችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምርኮ ምክንያት ወዳስለቀቅኋችሁም ምድር እመልሳችኋለሁ።”
እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቧል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ፤ ስለ ሕዝቦች አለቃ እልል በሉ፤ ምስጋናችሁን አሰሙ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ የእስራኤልን ቅሬታ፣ ሕዝብህን አድን’ በሉ።
ምርኳቸውን ስለምመልስላቸው በብንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፣ በይሁዳ ከተሞችና በተራራማው አገር ከተሞች፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች፣ መሬት በጥሬ ብር ይገዛል፤ ውሉም ተፈርሞ፤ በምስክሮች ፊት ይታሸጋል፤’ ይላል እግዚአብሔር።”
“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰውም ሆነ እንስሳት በማይኖሩበት በዚህ ባዶ ስፍራ፣ በከተማዎቹም ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት እንደ ገና ያገኛሉ።
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ያዕቆብን አሁን ከስደት እመልሰዋለሁ፤ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እራራለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።
የኔጌብ ሰዎች፣ የዔሳውን ተራራ ይይዛሉ፤ ከተራራው ግርጌ ያሉ ሰዎችም፣ የፍልስጥኤማውያንን ምድር ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንና የሰማርያንም ዕርሻ ይይዛሉ፤ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።
“ያዕቆብ ሆይ፤ በርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤ በጕረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታውም በሕዝብ ይሞላል።
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፤ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ። እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።
የሽባዎችን ትሩፍ፣ የተገፉትንም ብርቱ ሕዝብ አደርጋለሁ፤ ከዚያች ቀን አንሥቶ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ። ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ።”
የእስራኤል ቅሬታዎች ኀጢአት አይሠሩም፤ ሐሰትም አይናገሩም፤ በአንደበታቸውም ተንኰል አይገኝም። ይበላሉ፤ ይተኛሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።”
በዚያ ጊዜ እሰበስባችኋለሁ፤ ያን ጊዜ ወደ አገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ ዐይናችሁ እያየ፣ ምርኳችሁን በምመልስበት ጊዜ፣ መከበርንና መወደስን፣ በምድር ሕዝብ ሁሉ መካከል እሰጣችኋለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር።
ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ የተረፉትም ሕዝብ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ፣ የነቢዩንም የሐጌን መልእክት ሰሙ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ልኮታልና። ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።
“ለይሁዳ ገዥ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፣ ለሊቀ ካህናቱ ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፣ ከምርኮ ለተረፈውም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ እንዲህም ብለህ ጠይቃቸው፤
እርሷም በሞዓብ ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘና እህል እንደ ሰጣቸው በሰማች ጊዜ፣ ሁለቱን ምራቶቿን ይዛ ወደ አገሯ ለመመለስ ከዚያ ተነሣች።