ሶፎንያስ 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፣ የእግዚአብሔር የመዓት ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዝ ሳይወጣ፥ ቀኑም እንደ ገለባ ሳያልፍ፥ የጌታም ቁጣ ትኩሳት ሳይመጣባችሁ፥ የጌታም ቁጣ ቀን ሳይደርስባችሁ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አለበለዚያ ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው ገለባ ትሆናላችሁ፤ እንደ እሳት የሚነደው የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣባችኋል፤ ኀይለኛው የእግዚአብሔር የቊጣ ቀን ይመጣባችኋል። |
ሰዎቹ እንደ ኀይለኛ ውሃ ጩኸት ቢያስገመግሙም፣ እርሱ ሲገሥጻቸው፣ በኰረብታ ላይ በነፋስ እንደሚበንን ትቢያ፣ በዐውሎ ነፋስ ፊት እንደሚበተን ገለባ ይበተናሉ።
እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም።
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ሳይዘገይ ይፈጸማል፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ፤ የተናገርሁትን ሁሉ በዘመናችሁ እፈጽማለሁ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”
በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።” መላዪቱ ምድር፣ በቅናቱ ትበላለች፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለዚህ እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ አሕዛብን ላከማች፣ መንግሥታትን ልሰበስብ፣ መዓቴንና ጽኑ ቍጣዬን በላያቸው ላፈስስ ወስኛለሁ። በቅናቴ ቍጣ እሳት፣ መላዋ ምድር ትቃጠላለችና።