ስለዚህም እግዚአብሔር፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
ሶፎንያስ 1:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎች፣ የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤ ለክፉዎችም እንቅፋት የሆኑትን ጣዖታት አጠፋለሁ።” “ማንኛውንም ሰው ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፥ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሦች አጠፋለሁ፥ ክፉዎች እንዲደናቀፉ አደርጋለሁ፥ ሰውንም ከምድር ገጽ እቆርጣለሁ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎችንና እንስሶችን፥ የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን እደመስሳለሁ፤ ክፉዎች እንዲገለባበጡ አደርጋለሁ፤ የሰውን ዘር ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፥ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፥ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ስለዚህም እግዚአብሔር፣ “የፈጠርሁትን የሰው ዘር ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት እስከ ሰማይ ወፎች አጠፋለሁ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣ እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቅቃቸው፣ የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣ በዚያ ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ ይህም ኀጢአቱ የመወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።
እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤
ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።
“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች ዐዝናለሁ። ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።
ነገር ግን ሕዝቡን በጣዖቶቻቸው ፊት ስላገለገሏቸውና የእስራኤል ቤት በኀጢአት እንዲወድቅ ስላደረጉ፣ ስለዚህ የኀጢአታቸውን ዋጋ መቀበል እንዳለባቸው እጄን አንሥቼ ምያለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“ ‘ብራቸውን በየጐዳናው ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቈጠራል። በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ በኀጢአት እንዲወድቁ ዕንቅፋት ሆኖባቸዋልና በልተው አይጠግቡበትም፤ ሆዳቸውንም አይሞሉበትም።
አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”
ኤፍሬም ሆይ፤ ከእንግዲህ ከጣዖት ጋራ ምን ጕዳይ አለኝ? የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤ እኔ እንደ ለመለመ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው።”
“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው መሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን ያስተማረውን የበለዓምን ትምህርት የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ፤