ሩት 4:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የሟቹ ስም ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩ ደጅ እንዳይጠፋ፣ የሟቹን ስም በርስቱ ላይ ለማስጠራት የመሐሎን ሚስት የነበረችው ሞዓባዊት ሩትን አግብቼአታለሁ፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፥ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪም የሟቹ የማሕሎን ሚስት ሞአባዊቷ ሩት ሚስቴ ትሆናለች፤ ይህም ንብረቱ ከሟቹ ቤተሰብ እንዳይወጣና የትውልድ ሐረጉም ከወንድሞቹ መካከልና ከሀገሩ አደባባይ እንዳይጠፉ ያደርገዋል፤ ለዚህ ሁሉ ዛሬ እናንተ ምስክሮች ናችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፣ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገርም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፤” አላቸው። |
አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋራ ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወልድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስስ ነበር።
“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
እናንተም፣ “ለምን ይህ ሆነ?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ። ይህ የሆነው የትዳር ጓደኛህን፣ አጋርህንና የቃል ኪዳን ሚስትህን አታልለሃታልና፣ እግዚአብሔር በአንተና በወጣትነት ሚስትህ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምስክር ስለ ሆነ ነው።
ከነዓናውያንና ሌሎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ይህን ሲሰሙ ይከብቡናል፤ ስማችንንም ከምድር ገጽ ያጠፉታል፤ እንግዲህ ስለ ታላቁ ስምህ ስትል የምታደርገው ምንድን ነው?”
ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የአሊሜሌክን፣ የኬሌዎንንና የመሐሎንን ንብረት በሙሉ ከኑኃሚን ላይ ለመግዛቴ፣ በዛሬው ዕለት እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤