መዝሙር 96:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፣ ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቦች መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ለሕዝቦችም ሁሉ ታላቅ ሥራውን አውሩ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ነበልባሉም ጠላቶቹን ይከብባቸዋል። |
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፣ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣ የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤ የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።