መዝሙር 92:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ ለዘላለሙ ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማያስተውል ሰው አያውቅም። አላዋቂ አይረዳውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች እንደ ሣር ቶሎ ቢያድጉም፥ ክፉ አድራጊዎች ቢበለጽጉም፥ እነርሱ ለዘለዓለሙ ይጠፋሉ። |
የሕዝቦቻቸው ኀይል ተሟጥጧል፤ ደንግጠዋል፤ ተዋርደዋልም፤ በሜዳ እንዳሉ ዕፀዋት፣ እንደ ለጋ ቡቃያ፣ በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፣ በእንጭጩ ዋግ እንደ መታው ሆነዋል።
“እነሆ፤ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ ይሆናሉ፤ ያ የሚመጣው ቀንም ያቃጥላቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አያስቀርላቸውም።
ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል፣ “ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤