መዝሙር 92:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ፥ የአንተ ታላላቅ ሥራዎች ደስ ያሰኙኛል፤ አንተ ስላደረግኻቸውም ነገሮች በደስታ እዘምራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ውኆች ድምፅ የተነሣ የባሕር እንቅስቃሴዋ ድንቅ ነው። ድንቅስ በልዕልና የሚኖር እግዚአብሔር ነው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ፤ ስለ ሕዝቦች አለቃ እልል በሉ፤ ምስጋናችሁን አሰሙ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ የእስራኤልን ቅሬታ፣ ሕዝብህን አድን’ በሉ።
ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ በድል አድራጊነት እያዞረ ለሚመራን፣ የዕውቀቱንም መዐዛ በእኛ አማካይነት በየስፍራው ለሚገልጥ አምላክ ምስጋና ይሁን፤
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”