መዝሙር 90:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣ ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራህ ለአገልጋዮችህ ይታይ፥ ግርማህም ለልጆቻቸው ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ አገልጋዮችህ ታላቁን ሥራህን እንድናይ ፍቀድልን። ልጆቻችንም የኀይልህን ክብር እንዲያዩ አድርጋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤ በእኛ ዘመን አድሳቸው፤ በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን ዐስብ።
ይማረካሉ ያላችኋቸው ታናናሾች፣ ክፉና በጎውን ለይተው የማያውቁት ልጆቻችሁ ምድሪቱን ይገቡባታል፤ ለእነርሱም እሰጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሷታል።
“እነሆ፤ አሁን የምድርን ሁሉ መንገድ ልሄድ ነው፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ መልካም ተስፋ ሁሉ አንዲቱን እንኳ እንዳላስቀረባችሁ፣ በፍጹም ልባችሁ በፍጹም ነፍሳችሁ ታውቃላችሁ፤ አንዱም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሟል።