መዝሙር 88:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤ እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጆቼ ሁሉ ከእኔ እንዲርቁ አደረግህ፤ በፊታቸውም አጸያፊ አደረግኸኝ፤ ዙሪያዬ ታጥሮአል፤ ማምለጫም የለኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ የኀያላን አምላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እውነትም ይከብብሃል። |
እግዚአብሔር፣ ታዳጊ የሆነው የእስራኤል ቅዱስ፣ ለተናቀውና በሕዝብ ለተጠላው፣ የገዦች አገልጋይ እንዲህ ይላል፤ “ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤ ልዑላንም አይተው ይሰግዳሉ፤ ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ነው።”
“እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋራ አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቷል፤ ልብሴንም በክዬዋለሁ።
በዚያ ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ ተዘግቶበት ነበር።