መዝሙር 85:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤ በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፥ ከቁጣህ መቅሠፍት ተመለስህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤ በእኛም ላይ ያለህን ቅርታ አርቅልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና። |
በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ።
“የኤፍሬምን የሲቃ እንጕርጕሮ በርግጥ ሰምቻለሁ፤ ‘እንዳልተገራ ወይፈን ቀጣኸኝ፤ እኔም ተቀጣሁ። አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና፣ መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።
ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቍጣህን መልስ፤ በእኛ ኀጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።
የቍጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤ እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣ ሰው አይደለሁምና፣ በቍጣ አልመጣም።
በአካንም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታየውን ታላቅ የድንጋይ ቍልል ከመሩበት፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቍጣው ተመለሰ። ስለዚህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ያ ስፍራ የአኮር ሸለቆ ተባለ።