መዝሙር 80:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕሪያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤ በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፋታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዱር እርያዎች ይረጋግጡአታል፤ የበረሓ አራዊትም ይመገቡአታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤስ ቃሌን ሰምተውኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤ |
አንበሳ ከደኑ ወጥቷል፤ ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቷል፤ ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ ከስፍራው ወጥቷል። ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።
ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣ የምድረ በዳ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣ ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤ ዐመፃቸው ታላቅ፣ ክሕደታቸው ብዙ ነውና።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤
የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።
ነገር ግን በቍጣ ተነቀለች፤ ወደ ምድርም ተጣለች። የምሥራቅ ነፋስ አደረቃት፤ ፍሬዎቿንም አረገፈባት። ብርቱዎቹ ቅርንጫፎቿ ክው አሉ፤ እሳትም በላቸው።