ዐለቱን ሲመታ፣ ውሃ ተንዶለዶለ፤ ጅረቶችም ጐረፉ፤ ታዲያ፣ እንጀራንም መስጠት ይችላል? ሥጋንስ ለሕዝቡ ሊያቀርብ ይችላል?”
ዓለቱን መታ፥ ውኆችም ወጡ፥ ወንዞችም ጐረፉ፥ እንጀራን መስጠትስ ይችላልን? ለሕዝቡስ ማዕድን ያዘጋጃልን?”
አለቱን መሰንጠቁና ውሃም እንደ ጐርፍ ማፍሰሱ እውነት ነው፤ ታዲያ፥ ምግብን ሊሰጠን፥ ሥጋንም ሊያዘጋጅልን ይችላል ማለት ነውን?”
ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጡት።
“ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ነገ ሥጋ ትበላላችሁና ራሳችሁን በመቀደስ ተዘጋጁ። “በግብጽ ተመችቶን ነበር፤ አሁን ግን ሥጋ ማን ይሰጠናል!” ብላችሁ ያለቀሳችሁትን እግዚአብሔር ሰምቷል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ።
ድብልቁ ሕዝብ ሌላ ምግብ ጐመጀ፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ያጕረመርሙ ጀመር፤ “ምነው የምንበላው ሥጋ ባገኘን ኖሮ!
ከዚያም ሙሴ እጁን ዘርግቶ በበትሩ ዐለቱን ሁለት ጊዜ መታው፤ ውሃውም ተንዶለዶለ፤ ማኅበረ ሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።