ፍትሕ ማግኘቴን የሚወድዱ፣ እልል ይበሉ፤ ሐሤትም ያድርጉ፤ ዘወትርም፣ “የባሪያው ሰላም ደስ የሚለው፣ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
መዝሙር 70:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስም ይበላቸው፤ ማዳንህን የሚወድዱ ሁሉ ሁልጊዜ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሰይ እሰይ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ ሐሴትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ዘወትር “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ከኃጥኣን እጅ፥ ከዐመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ። |
ፍትሕ ማግኘቴን የሚወድዱ፣ እልል ይበሉ፤ ሐሤትም ያድርጉ፤ ዘወትርም፣ “የባሪያው ሰላም ደስ የሚለው፣ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስ ይበላቸው፤ ዘወትር የአንተን ማዳን የሚወድዱ፣ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።
አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው።
በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።