መዝሙር 70:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ፣ “ዕሠይ! ዕሠይ!” የሚሉ፣ ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጐስቁሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላኬና መድኀኒቴ ሁነኝ፤ ኀይሌና መጠጊያዬ አንተ ነህና። |
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፤ ‘የጌታ፣ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፣ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፣ የይሁዳም ቤት ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ፣ “ዕሠይ!” ብላችኋልና፣
“የሰው ልጅ ሆይ! ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም፣ ‘ዕሠይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች፤ ደጆቿም ወለል ብለው ተከፈቱልኝ፤ እንግዲህ እርሷ ስለ ፈራረሰች እኔ እከብራለሁ’ ብላለችና፤