መዝሙር 69:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጩኸት ደከምሁ፤ ጕረሮዬም ደረቀ፤ አምላኬን በመጠባበቅ፣ ዐይኖቼ ፈዘዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሰይ! እሰይ! የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። |
እንደ ጨረባ፣ እንደ ሽመላም ተንጫጫሁ፤ እንደ ርግብ አልጐመጐምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ሰማይ በመመልከት ደከሙ፤ ጌታ ሆይ፤ ተጨንቄአለሁና ታደገኝ!”
ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለባዕድ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ እጅህንም ለማንሣት ዐቅም ታጣለህ፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።
ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋራ አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።