መዝሙር 68:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት ማምለጥ የሚቻለውም በጌታ በእግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየዕለቱ የሚንከባከበን ጌታ የተመሰገነ ይሁን፥ እግዚአብሔር ያድነናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤ ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን ጌታ እግዚአብሔር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውነቴ ስድብንና ውርደትን ታገሠች፤ አዝኜ ተቀመጥሁ፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ። |
“እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
ነገር ግን ለይሁዳ ቤት እራራለሁ፤ በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶችና በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በእግዚአብሔር አድናቸዋለሁ።”
“እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።