ከዚያም አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ እንደ ገናም ልጅ ለመውለድ በቍ።
መዝሙር 6:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ደካማ ስለ ሆንኩ ምሕረት አድርግልኝ፤ ጌታ ሆይ! ደካማ ሰውነቴ እየተሠቃየ ስለ ሆነ፥ እባክህ ፈውሰኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ። |
ከዚያም አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ እንደ ገናም ልጅ ለመውለድ በቍ።
እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
“እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።