እንደ ውሻ እያላዘኑ፣ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤ በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።
በቁጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፥ የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደሚገዛ ይወቁ።
ጠላቶቼ በከተማይቱ ውስጥ እንደ ውሻ እያላዘኑ ሲልከሰከሱ ውለው፥ ወደ ማታ ይመለሳሉ።
ውሾች ከበቡኝ፤ የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤ እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።