መዝሙር 59:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአፋቸው ስለሚወጣው ኀጢአት፣ ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል፣ በትዕቢታቸው ይያዙ። ስለ ተናገሩት መርገምና ውሸት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንደበታቸው ኃጢአት አይጠፋም፤ ንግግራቸው ሁሉ ኃጢአት የሞላበት ነው፤ እነርሱ ስለሚራገሙና ስለሚዋሹ በትዕቢታቸው ይያዙ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤ እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል። |
ነገር ግን በሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ስለ ጸያፍ ተግባራቸው ይናገሩ ዘንድ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከሰይፍ ከራብና ከቸነፈር አተርፋለሁ። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣ በዚያ ቀን አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ ከእንግዲህ ወዲያ፣ በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም።