መዝሙር 56:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ ቃሎቼን ይጠመዝዙብኛል፥ በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተሰባስበው ይሸምቁብኛል፤ እርምጃዬን ሁሉ ይከታተላሉ፤ ሕይወቴንም ለማጥፋት ያደባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ሰውነቴንም አጐበጡአት፤ ጕድጓድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በውስጡም ወደቁ። |
“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።
በዚህ ምክንያት የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ ዳንኤል በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ ሊከስሱት ሰበብ ፈለጉ፤ ነገር ግን አላገኙበትም፤ ዳንኤል ታማኝ፣ ጠንቃቃና በሥራው እንከን የሌለበት ስለ ነበር፣ በርሱ ላይ ስሕተት ሊያገኙ አልቻሉም።
በዚህ ጊዜ ኢየሱስን የያዙት ሰዎች፣ የኦሪት የሕግ መምህራንና የሕዝብ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ ነበሩበት፣ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት።
ኢየሱስን አሳልፈው ለገዢው ኀይልና ሥልጣን ለመስጠት፣ ከአፉ በሚወጣ ቃል ለማጥመድ ይከታተሉት ነበር፤ ስለዚህም ጻድቃን መስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት።