መዝሙር 56:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፥ አንተ አምላኬ ከእኔ ጋር እንደሆንህ እነሆ፥ አወቅሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ከእኔ ጋር የሆነው እግዚአብሔር፥ ቃሉን የማመሰግነውና የማከብረው አምላክ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ ጽድቅህም እስከ ደመናት ድረስ። |
የሠረገላው አዛዦችም ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፣ “የእስራኤል ንጉሥ ይህ ነው” ብለው አሰቡ፤ ሊወጉትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ረዳው፤ አምላክም ከርሱ መለሳቸው፤
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።
ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ፣ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል።