መዝሙር 48:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፣ ብርቱ ምሽግ እንደ ሆናት አስመስክሯል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰሜን በኩል በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፥ እርሷም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤ እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም ዐሳብ ምክርን፥ |
እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያ መጣ፤ “ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ስላዋረዱ እታደጋቸዋለሁ እንጂ አላጠፋቸውም፤ ቍጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም።
በአጠገብሽ የሚያልፉ ሁሉ፣ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፤ “የውበት መደምደሚያ፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣ የተባለች ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ ራሳቸውን በመነቅነቅ፣ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያሾፋሉ።