መዝሙር 45:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልብሶችህ ሁሉ ከርቤና ሽቱ ዝባድም አሉ፥ በዝሆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶች ይልቅ የበገናና የመሰንቆ ድምጽ ደስ ያሰኙሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምድር ዳርቻ ጦርነትን ይሽራል፤ ቀስትን ይሰብራል፥ ጋሻንም ይቀጠቅጣል፥ በእሳትም የጦር መሣሪያን ያቃጥላል። |
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጕዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ሄደች፤ ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ፤ እጅ ከነሣትም በኋላ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ንጉሡም ለእናቱ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።
አንቺ የልዑል ልጅ ሆይ፤ ነጠላ ጫማ የተጫሙ እግሮችሽ፣ እንዴት ያምራሉ! ሞገስን የተጐናጸፉ ዳሌዎችሽ፣ ብልኅ አንጥረኛ የተጠበባቸውን የዕንሐብል ይመስላሉ።
ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ፣ እቴጌዎቻቸው ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽን ትቢያ ይልሳሉ፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔን ተስፋ የሚያደርጉም አያፍሩም።”
ሙሽራዪቱ የሙሽራው ናት፤ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን፣ የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል።
ሰባቱ የመጨረሻ መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፣ “ና፤ የበጉ ሚስት የሆነችውን ሙሽራ አሳይሃለሁ” አለኝ።